ወደ አማኞች ህብረት እንኳን ደህና መጡ! Leave a Comment / እንኳን ደህና መጡ / By Yene Wusane ወደ አማኞች ህብረት እንኳን ደህና መጡ! ጌታ አየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኝዎ አድርገው የተቀበሉ ከሆነ አዲስ ፍጥረት ሆነዋል፡፡ መጽሀፍ ቅዱስ በሁለተኛ ቆሮንቶሰ 5፡17 ላይ “ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል” ይላል፡፡ በተስፋ፣ በፍቅር በሰላምና እውነተኛ ስኬት የተሞላ አስደናቂ ጉዞም ጀምረዋል። የዚህ ብሎግ ገጽ አላማ በጀመሩት አዲስ መንገድ ሲሄዱ የሚረዳዎትን ሃሳቦች መጠቆምና እና ድጋፍ መስጠት ነው።!