የአጠቃቀም ውል
ተፈጻሚ የሚሆንበት ቀን ፡ እ.ኤ.አ. ዲሴምበር 14፣ 2024 (ታህሳስ 5 ቀን 2017 ዓ.ም.)
እንኳን ወደ My Great Decision – የኔ ታላቅ ውሳኔ – (“እኛ”፣ “የእኛ” ወይም “የእኛን”) በደህና መጡ። https://mygreatdecison.ca/ (“ድረ ገጹን”) በመድረስ ወይም በመጠቀም ፣ በዚህ የአጠቃቀም ውል ለመገዛት ተስማምተዋል። በዚህ ውል ውስጥ በተቀመጡት ዝርዝር ጉዳዮች ካልተስማሙ እባክዎ ድረ ገጹን አይጠቀሙ።
1. ውልን መቀበል
ይህንን ድረ ገጽ በመጠቀም፣ በአሉበት ሀገር ህግ መሰረት ለአካለ መጠን የደረሱ መሆንዎን አረጋግጠዋል፤ እናም ይህን የአጠቃቀም ውል እና ሁሉንም የሚመለከታቸውን የህግ ድንጋጌዎች ለማክበር ተስማምተዋል። ድረ ገጹን በድርጅት ስም እየተጠቀሙ ከሆነ፣ ድርጅቱን ወክለው በዚህ የአጠቃቀም ውልና ተያያዥ በሆኑ ህጎች ተስማምተዋል።
2. በውሉ ላይ የሚደረጉ ለውጦች
ይህን የአጠቃቀም ውል በማንኛውም ጊዜ የማሻሻል ወይም የማዘመን መብታችን የተጠበቀ ነው። ለውጦች ተፈጻሚጸነታቸው የሚጀምርበት ቀን ተገልጾ በዚህ ገጽ ላይ ይለጠፋሉ። ለውጦች ከተለጠፉ በኋላ ድረ ገጹን መጠቀም መቀጠል የተከለሱውን ውል መቀበልዎን ያረጋግጣል።
3. የተጠቃሚ መለያዎች
ሀ. መለያ መፍጠር
የድረ-ገጹን አንዳንድ ባህሪያት ለመድረስ መለያ መፍጠር ሊያስፈልግዎ ይችላል። ትክክለኛ፣ የተሟላ እና ወቅታዊ መረጃ ለመስጠት እና የመለያዎን መረጃ ለማዘመን ተስማምተዋል።
ለ. የመለያ ደህንነት
የመግቢያ ኮዶችንና መረጃዎችን ምስጢራዊነት የመጠበቅ ሃላፊነት አለብዎት እና በመለያዎ ስር ለሚደረጉ ሁሉም እንቅስቃሴዎች ሙሉ በሙሉ ሀላፊነት አለብዎት። ማንኛውንም ያልተፈቀደ ወይም አግባብ ያልሆነ አጠቃቀም ወዲያውኑ ያሳውቁን።
4. የተፈቀደ አጠቃቀም
ድረ ገጹን ለሕጋዊ ተግባራትና በእዚህ የአጠቃቀም ውል መሠረት ለተፈቀዱ ዓላማዎችና ተግባራት ብቻ ለመጠቀም ተስማምተዋል፡፡ እና የተከለከሉ አጠቃቀሞች የሚከተሉትን ያካትታሉ፣ በዚህ ብቻ ግን አይወሰኑም፦
ማንኛውንም ክልላዊ፣ ብሔራዊ ወይም ዓለም አቀፍ ህግ ወይም ደንብ መጣስ።
ጎጂ፣ ተሳዳቢ ወይም ህገወጥ ይዘትን ማስተላለፍ።
ወደ አልተፈቀደልዎት የድረ ገጹ ወይም ስርዓቶቹ መዳረሻ ለመግባት መሞከር።
የድረ-ገጹን ተግባር የሚያደናቅፍ፣ የሚያዛባ ወይም ጣልቃ የሚገባ ተግባር ላይ መሳተፍ።
5. አእምሯዊ ንብረት
ሀ. ባለቤትነት
በድረ-ገጹ ላይ ያሉ ሁሉም ይዘቶች፣ ጽሑፍ፣ ግራፊክስ፣ አርማዎች እና ሶፍትዌሮችን ጨምሮ በMy Great Decision ወይም በፍቃድ ሰጪዎቹ ባለቤትነት የተያዙ እና በአእምሯዊ ንብረት ህጎች የተጠበቁ ናቸው።
ለ. የተወሰነ ፈቃድ
ድረ ገጹን ለግል፣ ለንግድ ላልሆነ ዓላማ ለመጠቀም በብቸኝነት የማይዙት፣ የማይተላለፍ፣ ሊሻር የሚችል ፈቃድ ተሰጥቶታል።
6. በተጠቃሚዎች የቀረበ ይዘት
ሀ. በተጠቃሚ የመነጨ ይዘት
ይዘትን ወደ ድረ ገጹ በማስገባት (ለምሳሌ፡ አስተያየቶች፡ ግምገማዎች) ከድረ-ገጹ ጋር በተገናኘ በብቸኝነት የማይዙት፣ ከሮያሊቲ-ነጻ፣ በሁሉም አገሮች፣ ይዘቱን የመጠቀም፣ የማባዛት እና የማሳየት ዘላቂ ፍቃድ ሰጥተውናል።
ለ. የይዘት ኃላፊነት
ለሚያስገቡት ማንኛውም ይዘት እርስዎ ብቻ ኃላፊነቱን ይወስዳሉ። የሌሎችን መብት የሚጥስ ወይም ማንኛውንም ህግ የሚጥስ ይዘት ማስገባት የለብዎትም።
7. የዋስትናዎች ማስተባበያ
ድረ-ገጹ “ባለበት ሁኔታ” እና “ተደራሽ በሆነበት መጠን” ያለ ምንም አይነት በግልጽም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ሊሰጥ የሚችል ዋስትና፣ የቀረበ ነው፡፡. ድረ ገጹ ከስህተት የጸዳ፣ መቋረጥ የማይከሰትብት ወይም ደህንነቱ የተጠበቀ እንደሚሆን ዋስትና አንሰጥም።
8. የተጠያቂነት ገደብ
በሕግ በሚፈቀደው ከፍተኛ መጠን፣ በእርስዎ አጠቃቀም ወይም ድረ ገጹን መጠቀም ባለመቻሉ ለተከሰቱ ማናቸውም ጉዳቶች፣ ቀጥተኛ ያልሆነ፣ ድንገተኛ ወይም ቀጣይ ጉዳቶችን ጨምሮ ተጠያቂ አይደለንም።
9. ማካካሻ
ይህን የአጠቃቀም ውል በመጣስዎ ወይም በማናቸውም ህጎች ወይም የሶስተኛ ወገን መብቶች ጥሰት ምክንያት ለሚነሱ ማናቸውም የይገባኛል ጥያቄዎች፣ ኪሳራዎች ወይም ጉዳቶች My Great Decision የእኔን ታላቅ ውሳኔ እና ተባባሪዎቹን ለመካስ እና ምንም ጉዳት እንዳይደርስባቸው ለማድረግ ተስማምተዋል።
10. የሶስተኛ ወገን ማገናኛዎች
ድረ ገጹ የሶስተኛ ወገን ድረ ገጾችና ጣቢያዎች አገናኞችን ሊይዝ ይችላል። እነዚህ ማገናኛዎች ስራ ለማቅለል ወይም ምቾቶን ለመጠበቅ የቀረቡ ናቸው አንጂ አነዚህ አገናኞች በኛ ድረ ገጽ መካተታቸው አኛ ድጋፍና እወቅና እየሰጠናቸው ስለመሆኑ አያመለክትም። ለሶስተኛ ወገን ድረ-ገጾች ይዘት ወይም አሰራር ተጠያቂ አይደለንም።
11.ማቋረጥ
ይህን የአጠቃቀም ውል ከጣሱ ያለቅድመ ማስታወቂያ በኛ ውሳኔ የድረ-ገጹን መዳረሻ ልናቋርጥ ወይም ልናግድ እንችላለን።
12. ገዢ ህግ
ይህ የአጠቃቀም ውል የሚገዛው በካናዳ ህጎች ነው። በዚህ ውል ውስጥ የሚነሱ ማናቸውም አለመግባባቶች በካናዳ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ያገኛሉ።
13. የግንኙነት አድራሻ መረጃ
ይህን የአጠቃቀም ውል በተመለከተ ጥያቄዎች ወይም ስጋቶች ካሉዎት እባክዎን በሚከተለው አድራሻ ያግኙን፡
ኢሜል፡ mygreatdecision@gamail.com