እኛ ማን ነን?
“ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ”
ማርቆስ 16:15
ተልዕኮአችን
የኔ ታላቅ ውሳኔ – mygreatdecision.ca – ዓላማችን ማህበራዊ ሚዲያንና ድረ ገጽን ጨምሮ በልዩ ልዩ ዲጂታል ቻናሎች ወንጌልን በሁሉም የዓለም ማዕዘኖች ማዳረስ ነው። ግባችን ሁሉም ሰው የወንጌልን የምስራች የመስማት እድል እንዲኖረው ማድረግ ነው። ሰዎች ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኛቸው አድርገው እንዲቀበሉና የዘላለም ሕይወት ስጦታን እንዲያገኙ በእግዚአብሔር ጸጋና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን። ሰዎች ድጋፍ እና ማበረታቻ የሚያገኙበትን ኦንላይን አገልግሎቶችን በማቅረብ እምነታቸውን ለማሳደግና ወጌልን በተግባር እንዲኖሩ ለማበረታታት በትጋት እንሰራለን። አገልጋዮቻችን በሁሉም የአለም ማእዘናት የሚገኙ በመሆኑ የጊዜ ሰቅ (time zone) ሳይገድበን 24 ሰአት ተደራሽነት ይኖረናል፡፡
ያነጋግሩን
ከእርስዎ ለመስማት እንወዳለን። ጥያቄ አልዎት? ወይስ ስለ አገልግሎታችን ይበልጥ ለማወቅ ይፈልጋሉ? ያነጋገሩን። እኛን ለማግኘት እባክዎ ኢሜይል ይላኩልን ወይም በአድራሻ ገጽ ላይ ያለውን ቅጽ ይሙሉ፡፡ የእርስዎን ሀሳብ ለመስማትና ጥያቄዎን ለመመለስ ሁልጊዜም ዝግጁ ነን፡፡